ነፍሴ ሰላምን ዐጣች፤ ደስታ ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፣ “ክብሬ፣ ከእግዚአብሔርም ተስፋ ያደረግሁት ሁሉ ሄዷል” አልሁ። የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ ምሬትንና ሐሞትን ዐስባለሁ። ዘወትር አስበዋለሁ፤ ነፍሴም በውስጤ ተዋርዳለች። ሆኖም ይህን ዐስባለሁ፤ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው። ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።”
ሰቈቃወ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ሰቈቃወ 3
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሰቈቃወ 3:17-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos