ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሰው ከአንተ ጋራ ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን? ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል? እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር ዐስብ፤ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤ ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም። ንጽሕናህ መታመኛህ፣ ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን? “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ? እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣ መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
ኢዮብ 4 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢዮብ 4
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢዮብ 4:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos