ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሰው ከአንተ ጋራ ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን? ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል? እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር ዐስብ፤ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤ ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም። ንጽሕናህ መታመኛህ፣ ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን? “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ? እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣ መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ። በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ። አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤ የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሯል። ብርቱው አንበሳ ዐደን በማጣት ይሞታል፤ የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
ኢዮብ 4 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢዮብ 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢዮብ 4:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች