“ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ ከአርያም ሁሉን ከሚችል አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድን ነው? ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን? እርሱ መንገዴን አያይምን? ርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን? “በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ፣ እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣ እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ። አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣ የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ። “ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣ በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣ ሚስቴ የሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ ሌሎች ሰዎችም ይተኟት፤ ይህ አሳፋሪ፣ ፍርድም የሚገባው ኀጢአት ነውና። ይህ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ እሳት ነው፤ ቡቃያዬንም ባወደመ ነበር።
ኢዮብ 31 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢዮብ 31
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢዮብ 31:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos