የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢዮብ 30:20-26

ኢዮብ 30:20-26 NASV

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤ በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ። ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ። ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ። ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ። “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣ በርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም። በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን? ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን? ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።