ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። በማለዳም በቤተ መቅደስ አደባባይ እንደ ገና ታየ፤ ሕዝቡም በዙሪያው ተሰበሰበ፤ ሊያስተምራቸውም ተቀመጠ። የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በምንዝር የተያዘች ሴት አመጡ፤ በሕዝቡም ፊት አቁመዋት፣ ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር ተያዘች፤ ሙሴም፣ እንደዚች ያሉ ሴቶች በድንጋይ እንዲወገሩ በሕጉ አዝዞናል፤ አንተስ ምን ትላለህ?” ይህን ጥያቄ ያቀረቡለት፣ እርሱን የሚከስሱበት ምክንያት ለማግኘት ሲፈትኑት ነው። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ይጽፍ ጀመር። በጥያቄ ሲወተውቱት ቀና ብሎ፣ “ከእናንተ ኀጢአት የሌለበት እርሱ አስቀድሞ ድንጋይ ይወርውርባት” አላቸው። እንደ ገናም ጐንበስ ብሎ በምድር ላይ ጻፈ። ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። ኢየሱስም ቀና ብሎ፣ “አንቺ ሴት፣ ሰዎቹ የት ሄዱ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስም፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥሪ” አላት።
ዮሐንስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ዮሐንስ 8
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዮሐንስ 8:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos