ዮሐንስ 6:15-21

ዮሐንስ 6:15-21 NASV

ኢየሱስም ሰዎቹ መጥተው በግድ ሊያነግሡት እንዳሰቡ ዐውቆ እንደ ገና ብቻውን ወደ ተራራ ገለል አለ። በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፤ በጀልባውም ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሡ። ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር። ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር ባሕሩ ተናወጠ። ዐምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። እነርሱም እንዲሳፈር ፈለጉ፤ ጀልባዋም ወዲያውኑ ወደሚሄዱበት ዳርቻ ደረሰች።