ዮሐንስ 2:13-17

ዮሐንስ 2:13-17 NASV

የአይሁድ ፋሲካም እንደ ተቃረበ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በቤተ መቅደስ ውስጥ ከብቶችን፣ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡ እንዲሁም ተቀምጠው የገንዘብ ምንዛሪ የሚያከናውኑ ሰዎች አገኘ። የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ግቢ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችን ሳንቲም በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም፣ “እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “የቤትህ ቅናት ይበላኛል” ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው።