የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 63:7-9

ኢሳይያስ 63:7-9 NASV

የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣ እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣ አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ። እርሱም፣ “ርግጥ ነው፤ እነርሱ ሕዝቤ ናቸው፤ የማይዋሹኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው” አለ። ስለዚህም አዳኝ ሆነላቸው። በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም።