የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 54:14-17

ኢሳይያስ 54:14-17 NASV

በጽድቅ ትመሠረቻለሽ፤ የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤ የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤ አጠገብሽም አይደርስም። ማንም ጕዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጕዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል። “እነሆ፤ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣ የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ አንጥረኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።