አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤ በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ። ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ። ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። ሰሜንን፣ ‘አምጣ!’ ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣ በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”
ኢሳይያስ 43 ያንብቡ
ያዳምጡ ኢሳይያስ 43
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኢሳይያስ 43:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች