የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሆሴዕ 12

12
1ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤
ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤
ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል።
ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤
የወይራ ዘይትንም ወደ ግብፅ ይልካል።
2 እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤
ያዕቆብን#12፥2 ያዕቆብ ማለት ተረከዝ ይይዛል ማለት ሲሆን፣ ያታልላል ለማለት ዘይቤአዊ አገላለጽ ነው። እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤
እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
3በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤
ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ።
4ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤
በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣
እርሱንም በቤቴል አገኘው፤
በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤
5እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር
የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው።
6ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤
ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤
ዘወትርም በአምላክህ ታመን።
7ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤
ማጭበርበርንም ይወድዳል።
8ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤
“እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤
ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣
ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”
9“ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ፣#12፥9 ወይም በግብፅ ከነበራችሁበት ጊዜ አንሥቶ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤
በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣
እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ
አደርጋችኋለሁ።
10ለነቢያት ተናገርሁ፤
ራእይንም አበዛሁላቸው፤
በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።”
11ገለዓድ ክፉ ነው፤
ሕዝቡም ከንቱ ናቸው፤
ኮርማዎችን በጌልገላ ይሠዋሉን?
መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ፣
የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።
12ያዕቆብ ወደ ሶርያ#12፥12 ሰሜን መስጴጦምያን ያመለክታል ሸሸ፤
እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤
ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ።
13 እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣ፤
በነቢይም በኩል ተንከባከበው።
14ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤
ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤
ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

Currently Selected:

ሆሴዕ 12: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ