ዕንባቆም 2:2-4

ዕንባቆም 2:2-4 NASV

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንባቢው እንዲፈጥን፣ ራእዩን ግልጽ አድርገህ በጽላት ላይ ጻፍ። ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤ ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤ እርሱም አይዋሽም፤ የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤ በርግጥ ይመጣል፤ ከቶም አይዘገይም። “እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤ ምኞቱ ቀና አይደለም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ ይኖራል።