ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው ንግር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣ አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? “ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣ አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው? ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ? እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ ጠብና ግጭት በዝቷል። ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤ ፍትሕ ድል አይነሣም፤ ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣ ክፉዎች ጻድቃንን ይከብባሉ። የእግዚአብሔር “ቢነገራችሁም እንኳ፣ የማታምኑትን እናንተን፣ በዘመናችሁ አንድ ነገር ስለማደርግ፣ እነሆ፤ ሕዝቡን እዩ፤ ተመልከቱም፤ እጅግም ተደነቁ። የራሳቸው ያልሆኑትን መኖሪያ ስፍራዎች ለመያዝ፣ ምድርን ሁሉ የሚወርሩትን፣ ጨካኝና ፈጣን የሆኑትን፣ ባቢሎናውያንን አስነሣለሁ። እነርሱም የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው፣ ከራሳቸው ይወጣል። ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው። ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ። ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል አሞራ ይበርራሉ፤ ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ። ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል። ነገሥታትን ይንቃል፤ በገዦችም ላይ ያፌዛል፤ በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤ የዐፈር ቍልል ሠርቶም ይይዘዋል። ከዚያም በኋላ እንደ ነፋስ ዐልፎ ይሄዳል፤ ጕልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።”
ዕንባቆም 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ዕንባቆም 1
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዕንባቆም 1:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos