ገላትያ 4:28-31

ገላትያ 4:28-31 NASV

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ እናንተም እንደ ይሥሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። በዚያ ጊዜ እንደ ሥጋ ልማድ የተወለደው ልጅ፣ በመንፈስ ኀይል የተወለደውን አሳደደው፤ አሁንም እንደዚያው ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “ባሪያዪቱን ከነልጇ አባርራት፤ የባሪያዪቱ ልጅ ከነጻዪቱ ልጅ ጋራ አይወርስምና።” ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ የነጻዪቱ እንጂ የባሪያዪቱ ልጆች አይደለንም።