የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መክብብ 3:16-22

መክብብ 3:16-22 NASV

ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤ በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤ በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር። እኔም በልቤ፣ “ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣ እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል” ብዬ አሰብሁ። እንዲህም ብዬ አሰብሁ፤ “ሰዎች፣ እንደ እንስሳት መሆናቸውን ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል። የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው። ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደ ሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ። የሰው መንፈስ ወደ ላይ መውጣቱን፣ የእንስሳ እስትንፋስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር መውረዱን ማን ያውቃል?” ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው?