የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዳንኤል 1:12-20

ዳንኤል 1:12-20 NASV

“እባክህ አገልጋዮችህን ለዐሥር ቀን ያህል ፈትነን፤ ለመብል ከአትክልት፣ ለመጠጥም ከውሃ በስተቀር ምንም አይሰጠን፤ ከዚያም የእኛን መልክና የንጉሡን መብል የሚበሉትን ወጣቶች መልክ አስተያይ፤ በአገልጋዮችህ ላይ የወደድኸውን አድርግብን።” እርሱም በዚህ ነገር ተስማማ፤ ለዐሥር ቀንም ፈተናቸው። ከዐሥር ቀን በኋላም የንጉሡን መብል ከበሉት ከሌሎች ወጣቶች ይልቅ ጤናማዎችና ሰውነታቸው የወፈረ ሆነው ተገኙ። ስለዚህ መጋቢው ምርጥ የሆነውን ምግባቸውንና ሊጠጡት የሚገባውን የወይን ጠጅ አስቀርቶ በምትኩ አትክልት ሰጣቸው። እግዚአብሔር ለእነዚህ አራት ወጣቶች በማንኛውም ሥነ ጽሑፍና ትምህርት ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ማንኛውንም ራእይና ሕልም የመረዳት ችሎታ ነበረው። ወደ እርሱ እንዲመጡ ንጉሡ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ፣ የጃንደረቦቹ አለቃ ወደ ናቡከደነፆር አቀረባቸው። ንጉሡም ባነጋገራቸው ጊዜ ከመካከላቸው እንደ ዳንኤል፣ አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ ያለ ከቶ አልተገኘም፤ ስለዚህ በንጉሡ አገልግሎት ላይ ተሰማሩ። ንጉሡ በጠየቃቸው በማንኛውም የጥበብና የማስተዋል ጕዳይ በመላ ግዛቱ ካሉት አስማተኞችና ድግምተኞች ሁሉ ዐሥር እጅ በልጠው አገኛቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}