የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አሞጽ 1

1
1በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስ#1፥1 ዕብራይስጡ ዮአስ ያለው የኢዮአስ ተለዋጭ ስም ሳይሆን አይቀርም። ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየውና የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
2እርሱም እንዲህ አለ፤
እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤
ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጕዳል፤
የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል#1፥2 ወይም የእረኞች ሐዘን
የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጓል።”
በእስራኤል ጎረቤቶች ላይ የተሰጠ ፍርድ
3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣
ገለዓድን አሂዳለችና፤
4የቤን ሃዳድ ምሽጎች እንዲበላ፣
በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
5የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤
በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣
በአዌን#1፥5 አዌን የቃሉ ትርጕም ክፋት እንደ ማለት ነው። ሸለቆ ያለውን ንጉሥ#1፥5 ወይም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ፤
የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል”
ይላል እግዚአብሔር
6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣
ለኤዶም ሸጣለችና።
7ምሽጎቿን እንዲበላ፣
በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
8በአስቀሎና በትር የያዘውን፣
የአሽዶድንም ንጉሥ#1፥8 ወይም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰው
እስኪሞት ድረስ፣
እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤”
ይላል ጌታ እግዚአብሔር
9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም።
የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣
ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
10ምሽጎቿን እንዲበላ፣
በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
ርኅራኄን#1፥11 ወይም ሰይፍ ወይም ከርሱ ጋራ የተባበሩትን አጠፉ በመንፈግ፣
ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፤
የቍጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣
መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤
12የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣
በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
ድንበሩን ለማስፋት፣
የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀድዷልና።
14በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣
በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣
ምሽጎቿን እንዲበላ፣
በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
15ንጉሧ#1፥15 ወይም ሞሎክ በዕብራይስጡ ማልካም ይላል። ከሹማምቱ ጋራ፣
በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል፣”
ይላል እግዚአብሔር

Currently Selected:

አሞጽ 1: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ