በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየውና የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
እርሱም እንዲህ አለ፤
“እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤
ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጕዳል፤
የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤
የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጓል።”