2 ዜና መዋዕል 27
27
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም
27፥1-4፡7-9 ተጓ ምብ – 2ነገ 15፥33-38
1ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። እናቱም ኢየሩሳ የተባለች የሳዶቅ ልጅ ነበረች። 2አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ይሁን እንጂ እንደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር። 3ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር እንደ ገና ሠራው፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ። 4በይሁዳ ኰረብታዎች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ።
5ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊት#27፥5 3.4 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺሕ ቆሮስ#27፥5 2,200 ኪሎ ሊትር ያህል ነው። ስንዴና ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።
6ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።
7በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና የሠራቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። 8እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። 9ኢዮአታም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ አካዝም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።
Currently Selected:
2 ዜና መዋዕል 27: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.