የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ዜና መዋዕል 27

27
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም
27፥1-427፥7-9 ተጓ ምብ – 2ነገ 15፥33-38
1ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ ኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ስትሆን፣ ኢየሩሳ ትባል ነበር። 2አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን እንደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር። 3ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ። 4በይሁዳ ኰረብቶች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ።
5ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊት#27፥5 3.4 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺሕ ቆሮስ#27፥5 1,600 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ያህል ነው። ስንዴና ዐሥር ሺሕ ቆሮስ#27፥5 1,350 ሜትሪክ ቶን ገብስ ያህል ነው። ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።
6ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።
7በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና አካሄዱ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። 8በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ ኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። 9ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁ አካዝም በምትኩ ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ