ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ፣ ለራሱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ አዘዘ። እርሱም፣ የሚሸከሙ ሰባ ሺሕ፣ ከኰረብታ ላይ ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማንያ ሺሕ ሰዎችና ሦስት ሺሕ ስድስት መቶ የሥራ ተቈጣጣሪዎች አሰማራ። ከዚህ በኋላ፣ ሰሎሞን ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም የሚከተለውን ይህን መልእክት ላከ፤ “አባቴ ዳዊት የሚኖርበትን ቤተ መንግሥት ሲሠራ እንደ ላክህለት ሁሉ፣ ለእኔም የዝግባ ዕንጨት ላክልኝ። ሽታው ደስ የሚያሰኝ ዕጣን በፊቱ የሚታጠንበትን፣ የተቀደሰ እንጀራ በየጊዜው የሚቀርብበትን፣ በየጧቱና በየማታው፣ በየሰንበቱና በየመባቻው እንዲሁም በተወሰኑት በአምላካችን በእግዚአብሔር በዓላት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን ቤተ መቅደስ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ሠርቼ እቀድስ ዘንድ አስቤአለሁ። ይህም ለእስራኤል የዘላለም ሥርዐት ነው። “አምላካችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ስለ ሆነ፣ የምሠራውም ቤተ መቅደስ ታላቅ ይሆናል። ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ እንኳ እርሱን ይይዘው ዘንድ አይችልምና ቤተ መቅደስ ሊሠራለት የሚችል ማነው? በፊቱ ዕጣን የሚታጠንበትን እንጂ ቤተ መቅደስ እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
2 ዜና መዋዕል 2 ያንብቡ
ያዳምጡ 2 ዜና መዋዕል 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ዜና መዋዕል 2:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos