የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ተሰሎንቄ 3:6-13

1 ተሰሎንቄ 3:6-13 NASV

አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ መልካም ዜና አሰምቶናል። ደግሞም እኛን ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት የምንናፍቃችሁን ያህል እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነግሮናል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ በጭንቀታችንና በመከራችን ሁሉ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናናን። በጌታ ጸንታችሁ ስለ ቆማችሁ በርግጥ አሁን በሕይወት እንኖራለን። በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ምስጋና ልናቀርብ እንችላለን? እንደ ገና ልናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለማሟላት ሌሊትና ቀን እጅግ ተግተን እንጸልያለን። አሁንም ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅናልን። እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስ ያላችሁን ፍቅርና ለሌሎችም ያላችሁን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ፤ ያትረፍርፍላችሁም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ነቀፋ የሌለባችሁና ቅዱሳን ሆናችሁ እንድትገኙ ልባችሁን ያጽና።