የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 21:10-15

1 ሳሙኤል 21:10-15 NASV

በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ። የአንኩስ አገልጋዮችም፣ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ፣ “ ‘ሳኦል ሺሕ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺሕ ገደለ’ ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት። ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው። ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደ ሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፣ ልጋጉንም በጢሙ ላይ እያዝረበረበ እንደ እብድ ሆነ። አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሰውየውን እስቲ ተመልከቱት፤ እብድ እኮ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው? በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ ዐጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?”