1 ዜና መዋዕል 27
27
የሰራዊቱ ዋና ዋና ክፍሎች
1የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።
2በመጀመሪያው ወር፣ የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺሕ ሰዎች ነበሩ። 3እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።
4በሁለተኛው ወር፣ የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ አሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
5በሦስተኛውም ወር፣ የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፣ በሥሩ ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ። 6ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኀያል ሲሆን፣ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዓሚዛ ባድም የክፍሉ ሰራዊት አዛዥ ነበረ።
7በአራተኛው ወር፣ አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል ሲሆን፣ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
8በአምስተኛው ወር፣ አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
9በስድስተኛው ወር፣ ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
10በሰባተኛው ወር፣ ሰባተኛው የበላይ አዛዥ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
11በስምንተኛው ወር፣ ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊው ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
12በዘጠነኛው ወር፣ ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
13በዐሥረኛው ወር፣ ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
14በዐሥራ አንደኛው ወር፣ ዐሥራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፍሬም ወገን የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
15በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ ዐሥራ ሁለተኛው የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተ ሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ።
የየነገዱ የጦር ሹማምት
16የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤
በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤
በስምዖን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ።
17በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤
በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
18በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤
በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።
19በዛብሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤
በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ለኢያሪሙት።
20በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ፤
በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።
21በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል።
22በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።
23 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር። 24የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።
ንጉሡ የሾማቸው የበላይ ተቈጣጣሪዎች
25የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤
የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።
26የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።
27ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።
28ጌድራዊው በአልሐናን በምዕራባዊው ኰረብታዎች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ።
29ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤
የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።
30እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ።
ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።
31አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።
እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።
32አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
33አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።
34የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ።
ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
Currently Selected:
1 ዜና መዋዕል 27: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.