1 ዜና መዋዕል 26
26
የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች
1የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤
ከቆሬያውያን ወገን፤
ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም። 2ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤
የመጀመሪያው ዘካርያስ፣
ሁለተኛው ይዲኤል፣
ሦስተኛው ዝባድያ፣
አራተኛው የትኒኤል፣
3ዐምስተኛው ኤላም፣
ስድስተኛው ይሆሐናን፣
ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
4ዖቤድኤዶምም እንደዚሁ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤
የመጀመሪያው ሸማያ፣
ሁለተኛው ዮዛባት፣
ሦስተኛው ኢዮአስ፣
አራተኛው ሣካር፣
ዐምስተኛው ናትናኤል፣
5ስድስተኛው ዓሚኤል፣
ሰባተኛው ይሳኮር፣
ስምንተኛው ፒላቲ፤
እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።
6እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር። 7የሸማያ ወንዶች ልጆች፤
ዖትኒ፣ ራፋኤል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፤
ዘመዶቹ ኤሊሁና ሰማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።
8እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነርሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመሥራት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች በአጠቃላይ ስድሳ ሁለት ነበሩ።
9ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩት፤ ቍጥራቸውም በአጠቃላይ ዐሥራ ስምንት ነበረ።
10ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤
የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኵር ልጅ ባይሆንም እንኳ፣ አባቱ ቀዳሚ አድርጎት ነበር።
11ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካርያስ፤
የሖሳ ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶቹ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
12የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ ቤተ ዘመዶቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናወን ምድብ ተራ ነበራቸው። 13ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ።
14የምሥራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።
ከዚያም ምክር ዐዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።
15የደቡቡ በር ዕጣ ለአቢዳራ ሲወጣ፣ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።
16የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።
በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤
17በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፣
በሰሜን በኩል አራት፣
በደቡብ በኩል አራት፣
በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ጊዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።
18በምዕራቡ በኩል የሚገኘውን አደባባይ#26፥18 የዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም ግልጽ አይደለም። ደግሞ በመንገዱ ላይ አራት፣ በአደባባዩ#26፥18 የዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም ግልጽ አይደለም። ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።
19እንግዲህ የቆሬና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድል ይህ ነበር።
የግምጃ ቤት ኀላፊዎችና ሌሎች ሹማምት
20ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኀላፊ ነበረ።
21የለአዳን ዘሮች፣ በለአዳን በኩል ጌርሶናውያን የሆኑትና ለጌርሶናዊው ለለአዳን ቤተ ሰቦች አለቆች የሆኑት የለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣ 22የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኀላፊዎች ነበሩ።
23ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ከዑዝኤላውያን፤
24የሙሴ ልጅ የጌርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኀላፊ ነበረ። 25በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም፣ ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።
26ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ። 27በጦርነት ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት። 28ባለራእዩ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አበኔር፣ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የቀደሱትን ሁሉና እንዲሁም ሌሎቹን ንዋያተ ቅድሳት ሰሎሚትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።
29ከይስዓራውያን፤
ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።
30ከኬብሮናውያን፤
ለሐሻብያ፣ ጠንካራና ጐበዝ የሆኑ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሡም አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። 31በኬብሮናውያን በኩል በቤተ ሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ።
በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜር በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል። 32ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው።
Currently Selected:
1 ዜና መዋዕል 26: NASV
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.