የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ዜና መዋዕል 2

2
የእስራኤል ወንዶች ልጆች
2፥1-2 ተጓ ምብ – ዘፍ 35፥23-26
1የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ 2ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።
ይሁዳ
2፥5-15 ተጓ ምብ – ሩት 4፥18-22ማቴ 1፥3-6
እስከ ኤስሮን ወንዶች ልጆች
3የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤
ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ።
የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
4የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤
ይሁዳም በአጠቃላይ ዐምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
5የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤
ኤስሮም፣ ሐሙል።
6የዛራ ወንዶች ልጆች፤
ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ#2፥6 አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ አንዳንድ የዕብራይስጥ፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጆች (እንዲሁም 1ነገ 4፥31 ይመ) ግን፣ ዳራ ይላሉ።፤ በአጠቃላይ ዐምስት ናቸው።
7የከርሚ ወንድ ልጅ አካን#2፥7 አካን ማለት ችግር ወይም መከራ ማለት ነው።
እርሱም ዕርም የሆነ ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት#2፥7 የዕብራይስጡ ቃል አንድን ሰው ወይም ነገር ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን ያመለክታል። እንዲመጣ ያደረገ ነው።
8የኤታን ወንድ ልጅ፤
አዛርያ።
9የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤
ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።#2፥9 ዕብራይስጡ፣ ከሉባይ ይላል፤ ይኸውም የካሌብ ሌላው መጠሪያ ነው።
ከኤስሮም ልጅ ከአራም ጀምሮ ያለው የትውልድ ሐረግ
10አራም አሚናዳብን ወለደ፤
አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
11ነአሶን ሰልሞንን#2፥11 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም ሩት 4፥21) ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ሳልማ ወለደ፤
ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።
12ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤
ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።
13የእሴይ ወንዶች ልጆች፤
የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣
ሦስተኛ ልጁ ሳምዓ፣ 14አራተኛ ልጁ ናትናኤል፣
ዐምስተኛ ልጁ ራዳይ፣ 15ስድስተኛ ልጁ አሳም፣
ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።
16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ።
የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣሄል ነበሩ።
17አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።
የኤስሮም ልጅ ካሌብ
18የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤
ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን።
19ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሑርን ወለደችለት።
20ሑር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
22ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።
23ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት#2፥23 ወይም፣ የኢያዕርን መኖሪያ ነጠቁ
እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።
24ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት#2፥24 በዚህም ሆነ በቍጥር 42፣ 45፣ 49-52 ላይ፣ አባት ማለት፣ የአገር ሽማግሌ ወይም፣ የጦር መሪ ማለት ነው። አሽሑርን ወለደችለት።
የኤስሮም ልጅ ይረሕምኤል
25የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤
የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ። 26ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናም እናት ነበረች።
27የይረሕምኤል የበኵር ልጁ የራም ወንዶች፤
መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።
28የኦናም ወንዶች ልጆች፤
ሸማይና ያዳ።
የሸማይ ወንዶች ልጆች፤
ናዳብና አቢሱር። 29የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
30የናዳብ ወንዶች ልጆች፤
ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
31የአፋይም ወንድ ልጅ፤
ይሽዒ፣ ይሽዒም ሶሳን ወለደ።
ሶሳን አሕላይን ወለደ።
32የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤
ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
33የዮናታን ወንዶች ልጆች፤
ፌሌት፣ ዛዛ።
እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
34ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።
እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው። 35ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓታይ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
36ዓታይ ናታንን ወለደ፤
ናታንም ዛባድን ወለደ፤
37ዛባድ ኤፍላልን ወለደ፤
ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
38ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤
ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
39ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤
ኬሌስ ኤልዓሣን ወለደ፤
40ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤
ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
41ሰሎም የቃምያን ወለደ፤
የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
የካሌብ ጐሣዎች
42የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤
የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤
ዚፍም መሪሳን#2፥42 የዚህ ቃል የዕብራይስጡ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።
43የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤
ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።
44ሽማዕ ረሐምን ወለደ፤
ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ።
ሬቄም ሸማይን ወለደ፤
45ሸማይም ማዖንን ወለደ፤
ማዖንም ቤትጹርን ወለደ።
46የካሌብ ቁባት ዔፉ
ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች።
ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
47የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤
ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
48የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።
49እንዲሁም የማድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች።
ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
50እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።
የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤
ሦባል የቂርያትይዓይሪም አባት፤ 51ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጌድር አባት።
52የቂርያትይዓይሪም አባት የሦባል ዘሮች፤
የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤ 53እንዲሁም የቂርያትይዓይሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።
54የሰልሞን ዘሮች፤
ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን። 55በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች#2፥55 ወይም፣ ሶፍራውያን ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ