የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ዜና መዋዕል 16:8-15

1 ዜና መዋዕል 16:8-15 NASV

ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤ ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ። ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ ዘወትር ፊቱን ፈልጉ። ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤ እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣ እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች። እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤ ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።