አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ። የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት። የያፌት ወንዶች ልጆች፤ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ። የጋሜር ወንዶች ልጆች፤ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቴርጋማ። የያዋን ወንዶች ልጆች፤ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ። የካም ወንዶች ልጆች፤ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን። የኵሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ። የራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን። ኵሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ። ምጽራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣ የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂ ማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው። ከነዓን የበኵር ልጁ የሆነው የሲዶን እንዲሁም የኬጢያውያን፣ የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣ የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣ የአራዴዎያውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው። የሴም ወንዶች ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም። የአራም ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ። አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ። ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ በዘመኑ ምድር ስለ ተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ። ዮቅጣንም፣ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣ ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው። ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳላ፣ ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣ ሴሮሕ፣ ናኮር፣ ታራ፣ እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።
1 ዜና መዋዕል 1 ያንብቡ
ያዳምጡ 1 ዜና መዋዕል 1
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ዜና መዋዕል 1:1-27
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos