1
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:18
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፥ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፥ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:19
እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፥
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:17
ክፉ ማድረግን ተዉ፥ መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:20
እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:16
ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፥ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፥
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:15
እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፥ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:13
ምናምንቴውን ቍርባን ጨምራችሁ አታምጡ፥ እጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፥ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም፥ በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገሥም።
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:3
በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፥ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም።
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:14
መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፥ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሳቸውም ደክሜያለሁ።
Home
Bible
Plans
Videos