1
መጽሐፈ ምሳሌ 21:21
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ክብርን ያገኛል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 21:5
የትጉህ ዐሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 21:23
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 21:2
ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 21:31
ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ረድኤት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 21:3
ጽድቅንና ቅን ፍርድን ማድረግ መሥዋዕት ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 21:30
ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 21:13
ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።
Home
Bible
Plans
Videos