1
ኦሪት ዘኍልቍ 22:28
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔርም የአህያዪቱን አፍ ከፈተ፤ በለዓምንም፥ “ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው?” አለችው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘኍልቍ 22:31
እግዚአብሔርም የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርንም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት።
3
ኦሪት ዘኍልቍ 22:32
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ቀና አልነበረምና ላሰናክልህ ወጥቼአለሁ፤
4
ኦሪት ዘኍልቍ 22:30
አህያዪቱም በለዓምን፥ “ከወጣትነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ አንተን ቸል ያልሁበት፥ በአንተም እንዲህ ያደረግሁበት ጊዜ ነበርን?” አለችው። እርሱም፥ “እንዲህ አላደረግሽብኝም” አላት።
5
ኦሪት ዘኍልቍ 22:29
በለዓምም አህያዪቱን፥ “ስለዘበትሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር” አላት።
6
ኦሪት ዘኍልቍ 22:27
አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አየች፤ ከበለዓምም በታች ተኛች፤ በለዓምም ተቈጣ፤ አህያዪቱንም በበትሩ ደበደባት።
Home
Bible
Plans
Videos