1
ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:4-5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእናንተ ላይ የሕይወትን መንፈስ አመጣለሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:6
ጅማትንም እሰጣችኋለሁ፤ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ ቍርበትን እዘረጋለሁ፤ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
3
ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:3
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ታውቃለህ” አልሁ።
4
ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:1-2
የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ፤ አጥንቶችም በሞሉበት ሸለቆ መካከል አኖረኝ። በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አዞረኝ፤ እነሆም በሜዳው እጅግ ነበሩ፤ እነሆም እጅግ ደርቀው ነበር።
5
ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:7-8
እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፤ እነሆም መናወጥ ሆነ፤ አጥንቶችንም እየራሱ በሆነ በሰውነቱ ከአጥንቶች ጋር አንድ አደረጋቸው። እኔም አየሁ፤ እነሆም ጅማት ነበረባቸው፤ ሥጋም ወጣ፤ ቍርበትም በላያቸው ተዘረጋ፤ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።
Home
Bible
Plans
Videos