1
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ። አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
3
ኦሪት ዘፀአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
4
ኦሪት ዘፀአት 20:8
“የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ።
5
ኦሪት ዘፀአት 20:7
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
6
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ አህያህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርስዋ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
7
ኦሪት ዘፀአት 20:17
“የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።”
8
ኦሪት ዘፀአት 20:16
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
9
ኦሪት ዘፀአት 20:14
“አታመንዝር።
10
ኦሪት ዘፀአት 20:13
“አትግደል።
11
ኦሪት ዘፀአት 20:15
“አትስረቅ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች