1
መጽሐፈ መክብብ 5:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 5:19
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና ዕድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ፥ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
3
መጽሐፈ መክብብ 5:10
ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ብዙ እህልንም የሚወድድ እንዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው።
4
መጽሐፈ መክብብ 5:1
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
5
መጽሐፈ መክብብ 5:4
ፈቃዱ አይደለምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ አንተ ግን እንደ ተሳልህ ስእለትህን ስጥ።
6
መጽሐፈ መክብብ 5:5
ተስለህ የማትፈጽም ከሆነ ባትሳል ይሻላል።
7
መጽሐፈ መክብብ 5:12
ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአገልጋይ እንቅልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብልጽግናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚተወው የለም።
8
መጽሐፈ መክብብ 5:15
ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፤ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለው ምንም የለም።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች