1
መጽሐፈ መክብብ 3:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከፀሐይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 3:2-3
ለመፅነስ ጊዜ አለው፥ ለመውለድም ጊዜ አለው፤ ለመኖር ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው። ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤
3
መጽሐፈ መክብብ 3:4-5
ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው። ድንጋይን ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤
4
መጽሐፈ መክብብ 3:7-8
ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው።
5
መጽሐፈ መክብብ 3:6
ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤
6
መጽሐፈ መክብብ 3:14
እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘለዓለም እንዲኖር ዐወቅሁ፤ በእነርሱም ላይ መጨመር ከእነርሱም ማጕደል አይቻልም፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።
7
መጽሐፈ መክብብ 3:17
እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቁና በኀጢአተኛው ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል” አልሁ።
Home
Bible
Plans
Videos