1
መጽሐፈ መክብብ 2:26
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 2:24-25
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ። ያለ እርሱ ፈቃድ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ማን ነው?
3
መጽሐፈ መክብብ 2:11
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ፥ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
4
መጽሐፈ መክብብ 2:10
ዐይኖቼ ከፈለጉት ሁሉ አላጣሁም፥ ልቤንም ከደስታ ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ልቤ በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና፤ ከድካሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋንታዬ ሆነ።
5
መጽሐፈ መክብብ 2:13
እኔም ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ እንዲሁ ከአላዋቂ ይልቅ ለብልህ ብልጫ እንዳለው ተመለከትሁ።
6
መጽሐፈ መክብብ 2:14
የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ ናቸውና፤ አላዋቂ ግን በጨለማ ይሄዳል፤ ደግሞ የሁለቱም መጨረሻቸው አንድ እንደ ሆነ አስተዋልሁ።
7
መጽሐፈ መክብብ 2:21
ሰው በጥበብና በዕውቀት በብርታትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ዕድሉን ያወርሳልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም መከራ ነው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች