1
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:17
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:16
እርሱም፥ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” አለው።
3
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:15
የኤልሳዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነሥቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማዪቱ ዙሪያ ጭፍሮች ከተማዋን ከብበዋት አየ። ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናድርግ?” አለው።
4
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:18
ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነዚህን ሰዎች አሳውራቸው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል አሳወራቸው።
5
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:6
የእግዚአብሔርም ሰው፥ “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍራውንም አሳየው፤ ከእንጨትም ቅርፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ።
6
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:5
ከእነርሱም አንዱ ዛፉን ሲቈርጥ የምሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበር” ብሎ ጮኸ።
7
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 6:7
እርሱም፥ “እነሆ፥ ምሳርህ ውሰደው” አለ፤ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች