1
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:15
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እንዲህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ! ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:17
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
3
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:12
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
4
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:21
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
5
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:22
ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ኀይልን ሰጣቸው፤ እነርሱም ተመቱ።
6
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:3
ኢዮሣፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።
7
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:9
እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።
8
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:16
ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በአሲስ ዐቀበት ይወጣሉ፤ በሸለቆውም መጨረሻ በኢያርሔል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገኙአቸዋላችሁ።
9
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 20:4
ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ተሰበሰበ፤ ከይሁዳ ከተሞችም ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች