1
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:9
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ስለዚህም ሰምቶ በሕዝብህ ላይ መፍረድ ይችል ዘንድ፥ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ ለባሪያህ አስተዋይ ልቡና ስጠው፤ አለዚያማ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ ማን ይችላል?”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:12
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
3
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:11
እግዚአብሔርም አለው፥ “ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን፥ ባለጠግነትንም፥ የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና፥
4
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:13
ደግሞም ከነገሥታት የሚመስልህ ማንም እንዳይኖር ያልለመንኸውን ባለጠግነትና ክብር ሰጥቼሃለሁ።
5
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:14
አባትህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴ የሄድህ እንደ ሆነ፥ ዘመንህን አበዛልሀለሁ።”
6
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:5
እግዚአብሔርም በገባዖን ለሰሎሞን በሌሊት በሕልም ተገለጠለት፤ እግዚአብሔርም ሰሎሞንን፥ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ለምን” አለው።
7
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:7
አሁንም አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል፤ እኔም መውጫዬንና መግቢያዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።
8
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:10
ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።
9
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:6
ሰሎሞንም አለ፥ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ፥ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአባቴ ከባሪያህ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቈይተህለታል።
10
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 3:8
ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ፥ ስለ ብዛቱም ይቈጠር ዘንድ በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው።
Home
Bible
Plans
Videos