1
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:14
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋው አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጐድልም።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:1
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
3
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:13
ኤልያስም አላት፥ “በእግዚአብሔር እመኚ፤ አትፍሪ፤ ሄደሽም እንዳልሽው አድርጊ፤ አስቀድመሽ ግን ከዱቄቱ ለእኔ ታናሽ እንጎቻ አድርገሽ አምጭልኝ፥ ከዚያም በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ አድርጊ፤
4
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:12
ሴትየዋም፥ “አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፤ እነሆም፥ ጥቂት እንጨት እሰበስባለሁ፤ ሄጄም ለእኔና ለልጄ እጋግረዋለሁ፤ በልተነውም እንሞታለን” አለችው።
5
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:9
“ተነሥተህ በሲዶና አጠገብ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ በዚያም ተቀመጥ፤ እነሆም፥ ትመግብህ ዘንድ አንዲት መበለት አዝዣለሁ።”
6
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:16
በአገልጋዩ በኤልያስም ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዱቄቱ ከማድጋው አልተጨረሰም፤ ዘይቱም ከማሰሮው አልጐደለም።
7
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:15
እርስዋም ሄዳ እንዲሁ አደረገች፤ እርስዋና እርሱ ልጆችዋም በሉ።
8
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:10
ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማዪቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት መበለት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር፤ ኤልያስም ጠርቶ፥ “የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት።
9
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:4
ከፈፋው ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው አደረገ።
10
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:11
ውኃም ልታመጣለት በሄደች ጊዜ ወደ እርስዋ ጠርቶ፥ “እግረ መንገድሽን ቍራሽ እንጀራ በእጅሽ አምጭልኝ” አላት።
11
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:6
ቁራዎችም በየጥዋቱና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከፈፋውም ይጠጣ ነበር።
12
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:7
ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ፈፋው ደረቀ።
13
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:24
ሴቲቱም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ” አለችው።
14
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:5
ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ተቀመጠ።
15
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:22
እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የሕፃኑም ነፍስ ተመለሰች፥ ዳነም፤
Home
Bible
Plans
Videos