1
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:25-26
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እንዲሁም ኅብስቱን ከተቀበሉ በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፥ “አዲስ ሥርዐት የሚጸናበት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እንዲህ አድርጉ፤ በምትጠጡበትም ጊዜ አስቡኝ” አላቸው። ይህን ኅብስት በምትበሉበት፥ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታችን እስከሚመጣበት ቀን ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:23-24
ከእግዚአብሔር እንደ ተማርሁ አስተምሬአችኋለሁና፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ራሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት ኅብስቱን አነሣ። አመሰገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እንዲህም አላቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታሰቢያዬንም እንዲሁ አድርጉ።”
3
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:28-29
አሁንም ሰው ራሱን መርምሮና አንጽቶ ከዚህ ኅብስት ይብላ፤ ከዚህም ጽዋ ይጠጣ። ሳይገባው፥ የጌታችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያውቅ፥ ሰውነቱንም ሳያነጻ፥ የሚበላና የሚጠጣ ለራሱ ፍርዱንና መቅሠፍቱን ይበላል፤ ይጠጣልም።
4
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:27
አሁንም ሳይገባው ይህን ኅብስት የበላ፥ ይህንም ጽዋ የጠጣ የጌታችን ሥጋውና ደሙ ስለሆነ ዕዳ አለበት።
5
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 11:1
እኔ ክርስቶስን እንደምመስለው እኔን ምሰሉ።
Home
Bible
Plans
Videos