1
መጽሐፈ ምሳሌ 20:22
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ክፉ እመልሳለሁ አትበል፥ ጌታን ተማመን፥ እርሱም ያድንሃል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 20:24
የሰው አካሄዱ ከጌታ ዘንድ ነው፥ እንግዲስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?
3
መጽሐፈ ምሳሌ 20:27
የሰው መንፈስ የጌታ መብራት ነው የሆዱን ጉርጆች ሁሉ የሚመረምር።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 20:5
ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፥ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 20:19
ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 20:3
ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 20:7
ጻድቅ ያለ ነውር ይሄዳል፥ ልጆቹም ከእርሱ በኋላ ምስጉኖች ናቸው።
Home
Bible
Plans
Videos