1
መጽሐፈ ምሳሌ 16:3
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ሥራህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 16:9
የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፥ ጌታ ግን አካሄዱን ያቀናለታል።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 16:24
ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፥ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 16:1
የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፥ የምላስ መልስ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 16:32
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 16:18
ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 16:2
የሰው መንገድ ሁሉ በዐይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው፥ ጌታ ግን መንፈስን ይመዝናል።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 16:20
ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፥ በጌታ የታመነ ምስጉን ነው።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 16:8
በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።
10
መጽሐፈ ምሳሌ 16:25
ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፥ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።
11
መጽሐፈ ምሳሌ 16:28
ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፥ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።
Home
Bible
Plans
Videos