1
ወደ ዕብራውያን 2:18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ምክንያቱም እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ዕብራውያን 2:14
እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፥ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ እርሱም ዲያብሎስ ነው።
3
ወደ ዕብራውያን 2:1
ስለዚህ ከሰማነው ነገር ተንሸራትተን እንዳንወድቅ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባል።
4
ወደ ዕብራውያን 2:17
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
5
ወደ ዕብራውያን 2:9
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞትን እንዲቀምስ፥ ከመላእክት ለጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖ ኢየሱስን እናየዋለን።
Home
Bible
Plans
Videos