1
የዮሐንስ ራእይ 22:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የዮሐንስ ራእይ 22:12
“እነሆ! እኔ በቶሎ እመጣለሁ! ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምሰጠውን ዋጋ ይዤአለሁ፤
3
የዮሐንስ ራእይ 22:17
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።
4
የዮሐንስ ራእይ 22:14
ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።
5
የዮሐንስ ራእይ 22:7
ኢየሱስም “እነሆ! እኔ በቶሎ እመጣለሁ! የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚጠብቅ የተመሰገነ ነው!” አለ።
6
የዮሐንስ ራእይ 22:5
ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።
7
የዮሐንስ ራእይ 22:20-21
የእነዚህ ነገሮች ምስክር የሆነው “በእርግጥ፥ በቶሎ እመጣለሁ!” ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
8
የዮሐንስ ራእይ 22:18-19
እነሆ፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ነገር ቢጨምር፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች እግዚአብሔር ይጨምርበታል። ማንም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ነገር ቢያጐድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተነገሩት ከሕይወት ዛፍ ፍሬና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ድርሻውን ያጐድልበታል።
Home
Bible
Plans
Videos