1
መጽሐፈ መዝሙር 119:105
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መዝሙር 119:11
አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ።
3
መጽሐፈ መዝሙር 119:9
ወጣቶች ሕይወታቸውን በንጽሕና መጠበቅ የሚችሉት ትእዛዞችህን በመፈጸም ነው።
4
መጽሐፈ መዝሙር 119:2
ትእዛዞቹን የሚጠብቁ፥ በሙሉ ልባቸውም የሚፈልጉት፥ የተባረኩ ናቸው።
5
መጽሐፈ መዝሙር 119:114
አንተ ጋሻዬና መሸሸጊያዬ ነህ፤ በቃልህ ተስፋ አደርጋለሁ።
6
መጽሐፈ መዝሙር 119:34
ሕግህን ግለጥልኝ፤ እኔም አከብረዋለሁ፤ በሙሉ ልቤም እጠብቀዋለሁ።
7
መጽሐፈ መዝሙር 119:36
ሀብት ለማግኘት ከመስገብገብ ይልቅ ሕግህን የመፈጸም ፍላጎት እንዲኖረኝ አድርግ።
8
መጽሐፈ መዝሙር 119:71
ሕግህን እንድማር ስላደረገኝ መቀጣቴ መልካም ሆነልኝ።
9
መጽሐፈ መዝሙር 119:50
የተስፋ ቃልህ ሕይወቴን ስላደሰልኝ፥ በመከራዬ ጊዜ እንኳ እጽናናለሁ።
10
መጽሐፈ መዝሙር 119:35
ትእዛዞችህ ስለሚያስደስቱኝ እንድፈጽማቸው እርዳኝ።
11
መጽሐፈ መዝሙር 119:33
እግዚአብሔር ሆይ! የሕግህን ትርጒም አስተምረኝ፤ እኔም ዘወትር እከተለዋለሁ።
12
መጽሐፈ መዝሙር 119:28
ሐዘን በርትቶብኛል፤ በሰጠኸኝ የተስፋ ቃል መሠረት ኀይሌን አድስልኝ።
13
መጽሐፈ መዝሙር 119:97
ሕግህን እጅግ እወዳለሁ፤ ስለ እርሱ ቀኑን ሙሉ አስባለሁ።
Home
Bible
Plans
Videos