1
ትንቢተ ኤርምያስ 17:7-8
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“በእኔ ብቻ ተማምኖ የሚኖር ሰው ግን የተባረከ ነው። እርሱም በወራጅ ምንጭ አጠገብ እንደ ተተከለና በውሃም ውስጥ ሥር እንደ ሰደደ ዛፍ ይሆናል፤ ዘወትር ቅጠሉ ለምለም ሆኖ የሚኖር ይህ ዐይነቱ ዛፍ የፀሐይ ሐሩር እንኳ አያሰጋውም፤ ዝናብ ባይዘንብለትም እንኳ ፍሬ ከማፍራት አይገታም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኤርምያስ 17:9
“የሰው ልብ ከሁሉ ነገር በላይ ተንኰለኛና ጠማማ ነው፤ ውስጠ ምሥጢሩን የሚረዳ ማነው?
3
ትንቢተ ኤርምያስ 17:10
እኔ እግዚአብሔር ግን የሰውን አእምሮና የሰውን ልብ እመረምራለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው በአካሄዱና በሥራው መጠን ዋጋውን እሰጠዋለሁ።”
4
ትንቢተ ኤርምያስ 17:5-6
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ትቶ በሰው የሚታመንና፥ ‘ኀይል ይሆነኛል’ ብሎ በሥጋ ለባሽ ሰው የሚመካ የተረገመ ይሁን። እንዲህ ዐይነቱ ሰው ማንም ሊኖርበት በማይችል በጨው ምድርና በበረሓ እንደሚበቅል ቊጥቋጦ ነው፤ በሕይወቱ ሙሉ ምንም መልካም ነገርን አያገኝም።
5
ትንቢተ ኤርምያስ 17:14
እግዚአብሔር ሆይ፥ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ፤ ታደገኝ፤ እኔም በሰላም እኖራለሁ፤ ዘወትርም አንተን አመሰግናለሁ።
Home
Bible
Plans
Videos