1
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:2-3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ ይኖራል፤ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኀይል መንፈስ፥ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ በሚያየው ብቻ አይፈርድም፤ ወይም በሚሰማው ብቻ አይበይንም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:1
ግንድ እንደሚያቈጠቊጥና ከስሩም ቅርንጫፍ እንደሚያበቅል እንዲሁም ከእሴይ (ከዳዊት ንጉሣዊ) ዘር አንድ ንጉሥ ይወጣል።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:4
ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:5
ሕዝቡን የሚያስተዳድርበት የወገቡ መታጠቂያ እውነት፥ የጐኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:9
በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:6
ተኲላና በግ በአንድነት ይኖራሉ፤ ነብርም ከፍየል ግልገሎች ጋር አብሮ ይመሰጋል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል አብረው ይመገባሉ፤ ትንሽ ልጅም እየመራ ይጠብቃቸዋል።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 11:10
በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።
Home
Bible
Plans
Videos