1
መጽሐፈ መክብብ 1:18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ጥበብ በበዛ መጠን ትካዜ ይበዛል፤ ዕውቀትም በበዛ መጠን ጭንቀትን ያስከትላል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 1:9
ቀድሞ የሆነው ነገር እንደገና ይሆናል፤ አሁንም የሚደረገው ነገር ሁሉ ያው ቀድሞ የተደረገው ነው፤ ስለዚህ በመላው ዓለም አዲስ ተብሎ የሚጠራ ምንም ነገር የለም።
3
መጽሐፈ መክብብ 1:8
ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ አሰልቺነቱንም ሰው በቃል ገልጦ ሊናገረው እንኳ አይችልም፤ ዐይን አይቶ አይጠግብም፤ ጆሮም ሰምቶ በቃኝ አይልም።
4
መጽሐፈ መክብብ 1:2-3
ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ ሁሉ ነገር ከንቱ፥ እንዲያውም የከንቱ ከንቱ ነው፤ ሁሉም ነገር በፍጹም ከንቱ ነው። ሰው በሚኖርበት ዓለም በሥራ የሚደክምበት ነገር ሁሉ ትርፉ ምንድን ነው?
5
መጽሐፈ መክብብ 1:14
እነሆ በዚህ ዓለም ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ ተመለከትኩ፤ ይሁን እንጂ ሁሉ ነገር ከንቱ ሆኖ አገኘሁት፤ ሁሉም ነገር ነፋስን እንደ መጨበጥ ሆኖ ይቈጠራል።
6
መጽሐፈ መክብብ 1:4
ትውልድ አልፎ ትውልድ ይተካል፤ ምድር ግን ሳትለወጥ ለዘለዓለሙ ጸንታ ትኖራለች።
7
መጽሐፈ መክብብ 1:11
ባለፉት ዘመናት ተደርገው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ የሚያስታውስ የለም፤ ከእነርሱም በኋላ ተከታትለው የሚመጡትም ነገሮች ቢሆኑ በተተኪው ትውልድ ዘንድ መታሰቢያ አይኖራቸውም።
8
መጽሐፈ መክብብ 1:17
ስለዚህ ጥበብንና ዕውቀትን፥ እብደትንና ሞኝነትን ዐውቅ ዘንድ ኅሊናዬን አተጋለሁ፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ሆኖ አገኘሁት።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች